Lyrics

ደሞ እንድነቃ ዳግም ቆሜ አትመላለሽ መተሽ በልሜ የቀኑ ማማር ይበቃሻል ከተኛው አይኔ ምንቀርቶሻል አያንስም ለኔ ያንቺ ገላ ከፈርኦን ልጅ ከገሊላ ፍቅርሽ ባይሰጥም አሳልፎ አስቀርቶታል ልቤን ጠልፎ ዛሬስ መወደድ ላንቺ ነግቶልሻል የውበት ፀሀይ ወቶልሻል አዬ ጀምበር ሞላ አለም አጎንብሳ ያይንሽን ብሌን ውሀ ለብሳ ገጥሞሽ የሳባ ሞገስ የኪሊዮፓትራ አምረሽ ትታዪ ጀመር በራስሽ ተራ ባለም የውበት ፀሀይ ወቶ እንደገና ባንቺ ዘመን ላይ ዋለ ዛሬ ቁንጅና ያንስብሻል መባል ቆንጆ የማር ክዳኔ ከንፈርሽ ላይ ሰም አለ ወርቅ የፍቅር ቀኔ ያንስብሻል የኔ መልካም ያመል ሙዳይ ሰው አለወይ ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ (ውብ ፀባዬ ሰናይ ሰናይ) ሰናይ ፀባዬ ሰናይ ሰናይ ደሞ እንድነቃ ዳግም ቆሜ አትመላለሽ መተሽ በልሜ የቀኑ ማማር ይበቃሻል ከተኛው አይኔ ምን ቀርቶሻል አያንስም ለኔ ያንቺ ገላ ከፈርኦን ልጅ ከገሊላ ፍቅርሽ ባይሰጥም አሳልፎ አስቀርቶታል ልቤን ጠልፎ ዛሬስ መወደድ ላንቺ ነግቶልሻል የውበት ፀሀይ ወቶልሻል አዬ ጀምበር ሞላ አለም አጎንብሳ ያይንሽን ብሌን ውሀ ለብሳ ሆነሽ በመልክሽ ገዳይ የውበት አርበኛ ማሰብ አቃተን ባንቺ ተማርከን እኛ ወጥተን ባለም ከፍታ ምድሪቱን ባናይ የለም እንዳንቺ ቆንጆ ፀባዬ ሰናይ ያንስብሻል መባል ቆንጆ የማር ክዳኔ ከንፈርሽ ላይ ሰም አለ ወርቅ የፍቅር ቅኔ ያንስብሻል የኔ መልካም ያመል ሙዳይ ሰው አለውይ ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) አለወይ (ፀባዬ ሰናይ) ውብ እንዳንቺ ፀባዬ ሰናይ (ውብ ፀባዬ ሰናይ ሰናይ) ሰናይ ፀባዬ ሰናይ ሰናይ ፀባዬ ሰናይ ሰናይ
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out