Lyrics

አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት እዩዋት እዩዋት የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት በሏት በሏት አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት እዩዋት እዩዋት የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት በሏት በሏት ያካሄዷን ውበት የአለባበሷን ወጓን አድንቁልኝ የቆንጆዎች ቆንጆ እመቤት መሆኗን እወቁልኝ ኦሆ ውበት ልብን ያሳሳል ናፍቆቷን ልብን ያሳሳል ኦሆሆ እዩልኝ አፈጣጠሯን አሳሳቅ አነጋገሯን ኦሆሆ የፍልሰታ ህብስት አሀሀ የአጥብያ ንጋት መና የተለየች ፍጡር የአዳም ልጆች ብስራት የመስቀል ደመራ ኦሆ ችቦ ነደደባት የእንቁጣጣሽ ጀንበር የደረቷ ጥራት ተረከዘ ሎሚ ገዳይ ባቷ ኩሩ ዳሌ መቃ አንገቷ ኦሆሆ እንኮይ የመሰለው ፀደይ ፊቷ ሀሩ ፀጉሯ ሙት አንጀቷ በአለንጋ ጣቷ ጋሻ ህይወት ዳግም አድሳ የሰው ህግጋት ጥሳ ታድናለች ፈውሳ ፍቅር ነው መወደሷ አጀብ ያሰኛል ለሷ አጀብ ያሰኛል ለሷ አጀብ አጀባ አጀብ አጀባ አጀብ አጀባ አጀብ አጀብ አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት እዩዋት እዩዋት የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት በሏት በሏት አታምርም ወይ እስኪ ከልብ እዩዋት እዩዋት እዩዋት የቆንጆዎች ቆንጆ ውብ ነሽ በሏት በሏት በሏት ታደገኝ ሰዐቱ ጊዜ እና ዘመኑ ተለመነኝ ለሊቱ ረጭ ይበል ሳሞግሳት ልደር ደስ ይበለኝ ኦሆ ውበት ልብን ያሳሳል ናፍቆቷን ልብን ያሳሳል ኦሆሆ እዩልኝ አፈጣጠሯን አሳሳቅ አነጋገሯን ሀረግ ነው ዛላዋ ኦሆሆ ይጣራል ከርቀት የቋንቋዋ ብስለት አለው ልዩ ጥልቀት ጨዋታ ጌጧ ነው ኦሆሆ የለዛዋ ብቃት የሚያቃልል ጭንቀት ይሰጣታል ድምቀት የሂሩት ምሳሌ መሽቆጥቆጧ ያስጨንቃል ደግነቷ ኦሆሆ የኑሮ ፍሰሀ ቅንነቷ ያዋልላል ጨዋነቷ ኦሆሆ ሽንጧ በእውቅ የተሰራ ኮከብ ጥሯሷ ሲያበራ ፅልመት አስወጋጅ ጮራ ወደ ፅድቅ የሚያመራ ከንፈሯ እሸት ያፈራ አቤት አይኗ ሲጣራ አቤት አይኗ ሲጣራ አቤት አቤታ አቤት አቤቶ አቤት አቤቷ አቤት አቤቷ
Writer(s): Tsehaye Yohannes Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out